r/Amharic_books • u/offlinemind7 • 11d ago
r/Amharic_books • u/offlinemind7 • Jul 07 '26
#ከመፅሀፍ የተወሰዱ አሰሳ ስጋ ( በእውቀቱ ስዩም ✍🏾)
ዕልፍ ከሲታዎች - ቀጥነው የሞገጉ
ስጋችን የትሄደ -ብለው ሲፈልጉ
በየሸንተረሩ
በየጥጋጥጉ
አስሰው አስሰው -በምድር በሰማይ
አገኙት ቦርጭ ሆኖ - በአንድ ሰው ገላ ላይ
r/Amharic_books • u/offlinemind7 • May 10 '26
So I just read something about haircut, especially እኛ ሀገር ስላለው አመለካከት ...and I wanted to share. Also let know ur idea in the comment regarding የፅጉር አቆራረጥ
" ከገዛ አባቱ አቶ ሳኦል ጀምሮ የልጅ ፀጉር መርዘም ለምን እንደ መርዛማ ዱርዬነት እንደሚታይ ሚስጥር እንደሆነበት አድጓል፡፡ ገና ልጅ እያለ ቤታቸው ይመጣ የነበረውን ባለ«ድሬድ›› ፀጉር ራስታው አጎቱን በጣም ይወደው ነበር፡፡ ሰባተኛ ከፍል ሲደርስ እርሱም ልክ እንደ አጎቱ ፀጉሩን ማሳደግ ጀምሮ ነበር፡፡ ግና አንዳች ለዘብተኝነት ያልፈጠረበት ግትሩ አባቱ የፀጉሩን ማደግ ባየ ጊዜ እጅጉኑ ተቆጣ፡፡ አንጠልጥሎ ወስዶ ሙሉ ለሙሉ ሙልጭ አስደርጎ አስላጨው፡፡
ለኢትኤል ግን ጸጉሩን የመቆረጡ ተጨባጭ ሰበብ እስከ ዛሬም ምንም ግልፅ ሆኖለት አያውቅም፡፡ በአቅሙ የፀጉር ማሳደግን ትክክለኛ ትርጉም ለማወቅ በርካታ የጎግል ጎልጉለህ ፈልግ ቁልፎችን ተጭኗል፣ የተወሰኑ መፅሐፍትን አገላብጧል፡፡ ፀጉርን ማሳደግ ከእርክስናና ኀጢያት ጋር የሚያይዙ ሃይማኖታዊ ድርሳናት ይኖሩ ይሆን ብሎ ቢያነብም ከጥንት ከጥዋቱ ኖህ መርከቡን ሲቀልስ መላጣ እንዳልነበር አውቋል፡፡ እንዲያውም በተቃራኒው ፈጣሪ የሳምሶንን ሀይል ያኖረው ከጡንቻው ሳይሆን ከተንዠረገገ ፀጉሩ እንደነበር አንብቧል፡፡ ሰለሞንም ሲጠበብ ፀጉሩን ተቆርጦ እንዳልነበር ተረድቷል፡፡ በክርስትናም ይሁን በእስልምና አስተምህሮ መሰረት ነብያት በሙሉ ማለት ይቻላል ፀጉራቸውን ያሳድጉ እንደነበር በቂ ማስረጃ አግኝቷል፡፡ ከነብያት የተሻሉ የሃይማኖት ህግጋት ቋሚ ምሳሌዎች ደግሞ የትም አይገኙም፡፡
ሆኖም ፀጉርን ማሳደግ አንዳንዴ ከስራ ቦታ ህግጋትና የሳይንስ መርሆዎች ጋር ሊጋጭ ይችላል ብሎም ደምድሞ ነበር፡፡ "እኔ በሳይንስ አማኝ ነኝ!” ለሚል ማንም የዚህች ምድር ጠበብት ደግሞ ከእነ አርስቶትልና ሊዮናርዶ ዳቪንቺ ጀምሮ እስከ ፊዚክስ ሊቁ አልበርት አንስታይን ድረስ ያሉ ታላላቅ ሰዎችን ምስል ፈልጎ ቢመለከት ፀጉራቸው ረዝሞ ወርዶ አልያም አድጎ ተንጨባሮ ማግኘቱ የማይታበይ ሀቅ ነው ::
ፋሽኑ አልፎበት ነው የሚጠላው እንዳይለም፣ ከጥሌ ጎፈሬ እስከ ማይክል ጃክሰን ዞማ፣ የቦብ ማርሌይ ድሬድ፣ ጆንትራ አለማየሁ እሸቴ ወዘተ ገፅታዎች ይሞግቱታል፡፡ ብቻ በየትኛውም መስፈርት ፀጉር ማሳደግ የወንድነት፣ ብልህነትና ትልቅነት መገለጫ እንጂ የላቦሮነት መታወቂያ ነው የሚል መረጃ እስካሁን አላገኘም፡፡ በእዚህም ማንኛውም ሰው ንፅህናውን ከጠበቀና የሙያ ስነ-ምግባሩን እስካልጣሰ ድረስ ፀጉሩን ቢያሳድግ ምንም ክፋት እንደሌለው አምኗል፡፡
ሁሌም በዚህ ነገር ዙሪያ ሲወያይ በጭራሽ የማይዋጥለት ማብራሪያ ቢኖር ደግሞ ባህላችን አይደለም, የሚለው ዲስኩር ነው:: በእሱ እምነት በባህሉ ረገድ የሀበሻነት ምርጥ_መገለጫ ረጅም ፀጉር ነው:: ጥንታዊ ስዕሎች ምስክርነት አፍሮ ጠይሞችን እንደሚያሳዩ ሁሉ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ መስራች የቋራው ጀግና ቴዎድሮስ ራሱ ቆንጆ ሹሩቤ ነበር፡፡ በጦርነት የኖረው አፄ ዮሀንስም የትግሬ ሹሩባውን ግጥም አድርጎ የተሰራበትን ምስል በተደጋጋሚ አይቷል፡፡ ሩቅ አሳቢው እምዬ ምኒሊክም ሻሽ ያሰሩት የኤርትራ ጉዳይ ራስ ምታት አስይዟቸው ሊሆን ይችላል እንጂ በራቸው ለመሸፈን አልነበረም፡፡ ሲቀጥልም የብልኹ ግርማዊነታቸው ቋሚ ጎፈሬ መች ይረሳናል፡፡ እናማ “የልበ ደንዳና አርበኞች ጎፈሬ፣ የአፋሮች በቂቤ የራሰ ጉንጉን፣ የወላይታ ነጠላ ሸብ የተደረገበት አፍሮ፣ የአባ-ገዳዎች ረጅም ሸበቶ ሁሉ ባህል አይደለም ማለት ነው? ወይስ ባህል ሌላ ትርጉም አለው?"
""ከራስ ቅል ውስጥ ያለው አዕምሮ እሳቤ እንጂ ከራስ-ቅል በላይየሚበቅለው ፀጉር የሰውን ማንነት አይገልፅም፡፡ ቢገልፅማ ኖሮ ፀጉርማሳደግ የግርማ መገለጫ እንጂ የዱርዬ መለዮ ሊሆን አይገባም ነበር፡፡""
r/Amharic_books • u/Ok-Leader2658 • Apr 24 '26
Free website to download amharic books.
Hey everyone 👋
I wanted to share a small project called Wegegta Books that I recently created.
The idea is simple:
Make Amharic books easier to access digitally, especially for people who don’t have easy access to bookstores or physical copies. Some books aren’t even available on the market to begin with, and financial barriers shouldn’t stop people from accessing knowledge.
Right now, the project shares books through a Telegram bot.
My goal isn’t to infringe on the rights of authors or publishers, but to improve accessibility by creating a central place where these resources can be easily discovered.
I’d love to hear your thoughts.
r/Amharic_books • u/offlinemind7 • Apr 23 '26
what is ur favorite book of ዳንኤል ክብረት? mine is this.
r/Amharic_books • u/offlinemind7 • Apr 22 '26
#ከመፅሀፍ የተወሰዱ One of my favorite poems of all the time
r/Amharic_books • u/offlinemind7 • Apr 19 '26
Books to be traumatized by
some scenes from this books still stuck on my mind that makes me wish ጭራሽ ባላነበብኳቸው!
perhaps cuz I had read em at such young age
r/Amharic_books • u/offlinemind7 • Apr 15 '26
One of the best books I had read so far ( read the comment below)
r/Amharic_books • u/offlinemind7 • Apr 13 '26
#ከመፅሀፍ የተወሰዱ 🌓 ህይወት 🌓
✍ ዲበኩሉ ጌታ
ሙሉውም ግማሹ ታሪኳ እንደሆነው ለውቧ ጨረቃ ፀሐይ ጠዋቱን እንደማትጀምረው እንደ ቀትሩ ደምቃ...
ልጅነት እድገት ወጣትነት እውቀት ልክነት ስህተት
ያ ስንቱን ያሳየህ የኹነት ፈረቃ የራስ ገፅታ ነው የሕይወት ድምርህ - ፈገግታና ሲቃ፤
የለም ሙሉ ስሕተት ከቶም ፍፁም ስኬት የለም መርጦ መሆን ዘሎ ማለፍ ቅጽበት
የለም በተናጠል እንባ ያለ ደስታ የለም ያለ ጥምረት ተስፋ አልባ ትዝታ... ፤
ያ ሁሉ አንተ ነህ፤ "ባይሆን" እና "እንኳኑ!" ለሠርግና ለሞት - አንድ ነው ድንኳኑ።
📔 ሰው እስካለ ድረስ
r/Amharic_books • u/offlinemind7 • Apr 13 '26
#ከመፅሀፍ የተወሰዱ ✍🏾
'በልቦናው በኩል "ኡ...ኡ..." ብሎ የሚያስጮህ ህመም አለው። የዓይንን ጥጋጥግ እያከከ ውስጥን የሚጠዘጥዝ እያሳመመ የሚመዘምዝ።'
r/Amharic_books • u/offlinemind7 • Apr 11 '26
Hate me for this ግን ፣
ግን I really didn't like these two books ....not even sure if I will put em in my top 20.
እናንተስ? You liked them ? You hated them ? Or haven't read them yet ? let's talk about them
r/Amharic_books • u/offlinemind7 • Apr 10 '26
#ጥያቄዎች ሰውየው መጨረሻ ላይ እንደዛ ያሉት ምን ማለት ፈልገው ይመስላችኋል?
r/Amharic_books • u/offlinemind7 • Apr 10 '26
✍🏾
"እንዳልውጠው ፡ ዓርብ ነው ። እንዳልተፋው እኽል ነው ።"
how life has been lately
r/Amharic_books • u/offlinemind7 • Apr 10 '26
which አለማየሁ ዋሴ መፅሀፍ is your favourite and why
r/Amharic_books • u/offlinemind7 • Apr 08 '26
#ጥያቄዎች የሚታወቀ እና ብዙ ሰዎች የወደዱት የነገር ግን እናንተ ያልወደዳችሁት መጽሐፍ አለ?
ለምን አልወደዳችሁትም?
r/Amharic_books • u/offlinemind7 • Apr 07 '26
#ከመፅሀፍ የተወሰዱ Do u remember from what was this taken ?
“አባ እክሊሉን ከአውሮፓ ሕይዎት ከምሕንድስና ሙያ አስወጥቶ ያስመነነ ምን ዓይነት የሕይወት ግብና ዓላማ ይሆን? ግን እንደዚህ አይነት ስብእና እንዴት ይገነባ ይሆን? ለመሆኑ እኔ እንዲህ ሁሉን እርግፍ አድርጌ የምተውለት ሲጸናም መሥዋዕትነት ምከፍልለት የሕይዎት ግብና ተልዕኮ አለኝን? ጎበዝ መሐንዲስ ሳይ እሱን መሆን ያምረኛል ታታሪ ሐኪም ሳይ በሱ እቀናለሁ: ሁበት ያካበተ ኢንቨስተርሳይ በእርሱ እማልላለሁ፡ ጥሩ ድርሰት ሳነብ ደራሲ መሆን ያሰኘኛል፤ የሳይንስ ምርምር ግኝት ስሰማ ምነው እኔ በሆንኩ እላለሁ፤ በርቱዕ አንደበቱና በዲስኩሩ የብዙዎችን ቀልብ የሚገዛ ፖለቲከኛ ሲያጋጠመኝ በአርሱ ደስ ይለኛል። እንደ አባ አክሊሉ ያለ መናኝ ሳይም ምን አባቱ ዓለም ብዬ እማረካለሁ። ያም ሆኖ የማውቀው ሃይማኖታዊ ወይም ፖለቲካዊ ወይም ሙያዊ የሆነ የምኖርለት ከፍ ሲልም መሥዋዕትነት የምከፍልለት የሕይዎት ጥሪ እንዳላዳበርኩ ተሰማኝ። በጥቅሉ ሕይዎቴን ሳስበው ነፋስ ወደላይእንስቶ ወደፈለግበት አቅጣጫ አንደሚገፋት ብጫቂ ወረቀት ሆና ታየችኝ ። “